ኢትዮጵያ ዶላር መር የሆነው አለም አቀፍ የቦንድ ሽያጯ በእጅጉ መጨመሩ ተገለፀ፡፡


ኢትዮጵያ ዶላር መር የሆነው አለም አቀፍ የቦንድ ሽያጯ በእጅጉ መጨመሩ ተገለፀ፡፡
ሮይተርስ እንደዘገበው በተለያዩ አገራዊ የለውጥ ስራዎች ላይ የተጠመዱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በትላንትናው ዕለት ኢትዮጵያ ለሁለት አስርት ዓመታት በባላንጣነት ስታየው ከነበረው ከኤርትራው መሪ ፕሬዝዳንት ኢሳስ አፈወርቂ ጋር ከስምምነት መድረሳቸውን ተከትሎ ባለፉት ሶስት ሳምንታት ባልታየ መልኩ የኢትዮጵያ የዶላር ቦንድ ገበያ ከፍተኛ ጭማሬ አሳይቷል፡፡
ይህም ባለፉት 10 ሳምንታት ውስጥ ከታዩት የቦንድ ሽያጭ ዋጋ ከፍተኛው ሆኖ እንዲመዘገብ አስችሎታል ብሏል ዘገባው፡፡
ሮይተርስ ቶምሰን ፋውንዴሽን የቦንድ ግብይት ገበያ መረጃውን ተንተርሶ ይፋ ባረገው መረጃ የኢትዮጵያ የቦንድ ሽያጭ ዋጋ በ$0.583 ሳንቲም ጭማሬ አሳይቷል፡፡ይህም ካለፈው ረቡዕ ወዲህ አንድ የኢትዮጵያ የዶላር ቦንድ ሽያጭ ሶስት ዶላር ጭማሬ እንዲያሳይ አድርጎታል ብሏል፡፡
ዝቅተኛው አንድ ኢትዮጵያ ቦንድ በአለም አቀፍ ገበያ 100.25 የአሜሪካን ዶላር ማስመዝገቡም ተመልክቷል፡፡
የኢትዮጵያና ኤርትራ መሪዎች የፊት ለፊት ምክክር እና ስምምነት እውን መሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ስልጣን ሲመጡ የሰላም ጠሪ ማቅረባቸውን ተከትሎ ነው፡፡
በኬንያ የስታኒክ ባንክ እና የምስራቅ አፍሪካ ከፍተኛ የምጣኔ ሀብት ባሙያ የሆኑት ጂብራን ቁረይሺ ለሮይተርስ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ አለም አቀፍ የቦንድ ሽያጭ እድገት ያሳየው በአገሪቱ እየተወሰደ ያለው ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎችን ተከትሎ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያ ቦንድ የተሻለ ፍላጎትና መተማመን ስላደረባቸው ነው፡፡
ምንጭ፡ ሮይተርስBack to Home

More Events ..


Ethiopia, Eritrea inked MoUs on some major areas of cooperation Read More


ኢትዮጵያ ዶላር መር የሆነው አለም አቀፍ የቦንድ ሽያጯ በእጅጉ መጨመሩ ተገለፀ፡፡ Read MoreVISITOR COUNT
TODAY COUNT:   76
THIS WEEK:   263
THIS MONTH:   1494
THIS YEAR:   9365
TOTAL:    24585
         Services
      * Visa Service
      * Document Authentication
      * For Diplomatic Community
      * For Bussiness Community
      * Government E-Services
         Media
      * Week in the Horn
      * Press Release
      * Speech
      * Articles

Subscribe Our News Posts